እንኳን ወደ ኦሮሚያ፤ቱባ ባህል፤ታሪክ እና እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ባለቤት፤ ብርቅዬ የዱር እንስሳት እና የአዕዋፋት ምድረ ገነት በሰላም መጣችሁ!
ክልላችን ኦሮሚያ ማራኪና ዉብ የተፈጥሮ ሃብት ፤ምቹ የአየር እና መልካምድር አቀማመጥ ባለቤት ፤ አስደናቂ የባህል ፤ታሪክና በተፈጥሮ መስቦቿ የምትማርክ ፤ምንግዜም አረንጓዴና ለምለም፤ናት ኦሮሚያ፡፡
ክልላችን ብርቅዬ የዱር እንስሳት እና የአዕዋፋት ምድረ ገነት እና በህብረቀለማት ያሸበረቀ የኦሮሞ ህዝብ ባህል ፤ታሪክ እና እሴቶች ፤በተጨማሪም የመቻቻል ባህላችን ፤እንግዳ ተቀባይነታችን እና የኦሮሞ ህዝብ ለብዙ ሺ ዓመታት የምትታወቅበት የዘመናዊዉ የዲሞክራሲ ስርዓት አስተዳደር ጅማሮ ምንጭ የሆነዉ የኦሮሞ ህዝብ የገዳ ስርዓት አስተዳደር አንድ ላይ ተደምሮ ኢትዮጵያ በአለም ደረጃ ከፍ ብላ እንድትታይ ከማድረጉም በላይ ክልላችን ኦሮሚያን በዉበት ላይ ዉበት በመላበስ በሰዉ ልጆች ልቦና ዉስጥ የክልሉን ጥሩ ገፅታ እንዲኖር በማድረግ የቱሪስት መዳረሻነቷ ገዝፎ ትልቅ የእንግዶች ማረፊያ እንድትሆን አስችሏታል፡፡
ሌላኛዉ የኦሮሚያ ክልል ድንቅ መስብ ደግሞ በዓለማችን ትልቁና ድንቅ ዋሻ የሆነዉ የሶፍ ዑመር ዋሻ ፤በስፋትና በግዝፈቱ ታዋቂ የሆነዉ የአፍሪካ ፓርክ መገኛ ፤ብርቅዬና ድንቅ የተፈጥሮ ሀብት መነሃሪያ ፤የዱር እንስሳት እና የአዕዋፋት ምድረ-ገነት በመባል የሚታወቀዉ የባሌ ብሔራዊ ፓርክ ፤የሰዉ ልጅ ዘር መገኛ ተብሎ ከሚታወቁ አከባቢዎች አንዱ የሆነዉ የመልካ ቁንጡሬ አርክዮሎጂካል ስፍራ በተጨማሪም የተለያዩ ዕድሜ ጠገብ የሆኑ ገዳማት ፤መሳጅዶች ፤ ቤተመንግስቶች እና የአለማችን የዲሞክራሲ ምንጭ ጅማሮ የሆነዉ የኦሮሞ ህዝብ የገዳ ሥርዓት እና ሌሎችም የተፈጥሮ መስቦቻችን በሃገራችን ኢትዮጵያም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ልዩና ተመራጭ የቱርስት መዳረሻ ያደርጉናል !
ኖሩ! አናዱፉ ብለናል!
ድህረ ገፃችንን ስለጎበኛችኁት በቅድሚያ እናመሰግናለን
የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ