foto1
foto1
foto1
foto1
foto1

Oromia Culture and Tourism Bureau

Biiroo Aadaafi Tuurizimii Oromiyaa

                                                                        Afaan Oromoo                                                                     English

አላማ
በክልላችን የሚገኙ የባህል እና የቱሪዝም ተsማት የሚሰጡትን አገልግሎት ጥራት በመጨመር የደንበኞችን እርካታ ጨምሮ የተቋሙ ገቢ እንዲጨምር እና በሀገር ደረጃ ከሴክተሩ የሚገኘው ገቢ እንዲጨምር ማድረግ ነው፡፡ 

መግለጫ
የባህል እና የቱሪዝም ተቋማት ስንል፡-
1. የባህል ተቋማት ለምሣሌ (ቤተ መጻሕፍት፣ ሙዚየም፣ ሲኒማ ቤት፣ ሙዚቃ ቤት የባህል ዕቃ መሸጫ እና የመሣሠሉት)
2. የቱሪዝም /የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ/ ተቋማት (ሆቴል፣ ሎጅ፣ ሬስቶራንት፣ ሞቴል፣ ካፊቴሪያ፣ ፔኒሲዮን፣ ሪዞርት፣ ቱርጋይድ፣ የፈረስ ግልቢያ ኪራይ እና የመሣሠሉት)


የምንሰጠው አገልግሎት
1.    የባህል እና የቱሪዝም ተቋማትን መከታተል፣ ሙያዊ ድጋፍ መስጠት እና ቁጥጥር ማድረግ
2.    የሴክተሩን ባለሙያዎች፣ የባህል እና የቱሪዝም ተቋማት ሠራተኞች የአገልግሎት አሰጣጥ ብቃታቸውን ለማሣደግ የተለያየ ስልጠና መስጠት
3.    ለባህል እና ቱሪዝም ተቋማት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሠርቲፊኬት መስጠት እና የእድሣት አገልግሎት መስጠት
4.    ከቀረጥ ነፃ/ማበረታቻ/ እንዲያገኙ ለባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር የድጋፍ ደብዳቤ መፃፍ
5.    የባህል እና የቱሪዝም ተቋማትን መረጃ በመያዝ ማጠናቀር
6.    የቱሪስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት/ሆቴሎች/ ደረጃ ውስጥ ያሉ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ እና ደረጃ ውስጥ ያልገቡ ደረጃ ውስጥ እንዲገቡ ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ'


ከቀረጥ ነፃ/ማበረታቻ/ የሚያስገኝ የድጋፍ ደብዳቤ ለማፃፍ፡-
ላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፡-
1. የኢንቨስትመንት ፈቃድ
2. የግንባታ ፈቃድ/ለሆቴል፣ ለሎጅ፣ ለሬስቶራንት፣ ለሞቴል/
3. የባለቤትነት/የይዞታ/ ማረጋገጫ
4. የመመስረቻ ጽሁፍ እና የመተዳደሪያ ደንብ ኃ.የተ.የግል ማህበር ወይም የህብረት ሥራ ከሆነ
5. ድርጅቱ በደረጃ ሊታቀፍ እንደሚችል ከሚገኝበት ዞን ወይም ከተማ ከሴክተሩ ጽ/ቤት የተፃፈ ማረጋገጫ