foto1
foto1
foto1
foto1
foto1

Oromia Culture and Tourism Bureau

Biiroo Aadaafi Tuurizimii Oromiyaa

                                                                        Afaan Oromoo                                                                     English

ክትትል እና ቁጥጥር


የባህል እና የቱሪዝም ተቋማት የሚሰጡት አገልግሎት ብቃት እንዲጨምር፡-

የባህል እና ቱሪዝም ተቋማት አገልግሎት ማብቃት ዋና የሥራ ሂደት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ውጤቶች ላይ ማዕከል በማድረግ የባህል እና የቱሪዝም ተቋማትን ክትትል እና ቁጥጥር ያደርጋል፡፡

  •  የሴክተሩን ባለሙያዎች፣ የባህል እና ቱሪዝም ተቋማት ሠራተኞችን የአገልግሎት አሰጣጥ ብቃት በመከታተል ባለው ክፍተት ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ የአገልግሎት እንዲሻሻል ከውስጥም ሆነ ከውጭ አካላት ጋር በመሆን ስልጠና መስጠት
  • ታሪካዊ እና ተፈጥሮአዊ የቱሪስት ተቋማት እና ሀብቶችን በመንከባከብ እንዲጠበቁ መከታተል እና ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ
  • በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሠርቲፊኬት እንዲያወጡና በወቅቱ ዕድሣታቸውን እንዲያከናውኑ መከታተል
  • የባህል እና ቱሪዝም ተቋማትን መረጃ ለመያዝ እና ለማጠናቀር
  • የቱሪስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት/ሆቴሎች/ ደረጃ ውስጥ ያሉ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ እና ደረጃ ውስጥ ያልገቡ ደረጃ ውስጥ እንዲገቡ መከታተል፡ ሙያዊ ድጋፍ መስጠት እና ቁጥጥር ማድረግ ሲሆን፡-

በዚሁ መሠረት የባህል እና ቱሪዝም ተቋማት አገልግሎት ማብቃት ዋና የሥራ ሂደት እስከ አሁን 7,108 ለሚሆኑ ሙያዊ ድጋፍ፣ ክትትል እና ቁጥጥር አድርጓል፡፡
95 ለሚሆኑ በአስጎብኚ አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ ተቋማት/ማህበራት/የመከታተል፣ ሙያዊ ድጋፍ የመስጠት እንዲሁም የቁጥጥር ስራ ተሰርል፡፡